Mon - Fri 08:00 AM- 05:00 PM | Sat 08:00 AM- 12:00 PM+251 11 557 12 04
info@ethswitch.com | Career

ኢትስዊች አ.ማ. የዲጂታል ክፍያ ግብይቶችን ለማሳደግ የሚያስችለውን ተጨማሪ ካፒታል አጸደቀ!

(መጋቢት 7/2015 ዓ.ም አዲስ አበባ) የኢትስዊች አ.ማ. 6ተኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን የኩባንያው ባለአክሲዮኖች በተገኙበት በሸራተን አዲስ ተካሄደ፡፡ ጉባዔው የተጠራው ኩባንያው የተሻሻለውን የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ እውን ለማድረግ፣ የንግድ ሥራውን እና የጋራ መሠረተ ልማት ለማሟላት፣ የፋይናንስ አቅምን ለማሻሻል፣ አዲስ ሕንፃ ለመገንባት እና አዳዲስ ዕቅዶችን ለማዳበር ብሎም ለመተግበር የሚያስችል ተጨማሪ ካፒታል በማስፈለጉ ነው።

 

የኢትስዊች አ.ማ.  ሊቀመንበር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ደስታ ጉባዔውን ሲከፍቱ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት “አክሲዮን ማህበሩ የአምስት ዓመት ስትራቴጂውን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተቀመጠው ክፍያን የማዘመን ሂደት ጋር በማስተሳሰር በፖሊሲ ዘርፍ፣ በገቢ ማስገኛ እንዲሁም በኦፕሬሽን ሥራዎች ላይ ከፍተኛ ስኬት እያስመዘገበ የሚገኝ ኩባንያ ነው” ብለዋል፡፡

አቶ ሰለሞን አያይዘውም “ኩባንያው በሁሉም አባል የፋይናንስ ተቋማት ዘንድ ተናባቢነትን በማስፋት፣ የክፍያ ስርዓትን የጋራ መሠረት ልማት አገልግሎቶችን በማሳደግና የውስጥ አቅምን በማጎልበት አስተማማኝ እና እንከን የለሽ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የስትራቴጂ ለውጦችን አድርጓል” ብለዋል፡፡

አቶ ሰለሞን እንዳብራሩት ለሥራው የሚያስፈልገውን መሰረተ ልማቶችን ለማበልጸግ የሚደረገው እንቅስቃሴ ኩባንያውን ለመቀላቀል ፍላጎት ያላቸውን አዲስ የሚመጡ ባንኮች ለማካተት የሚያስችል እንደሆነና የነባር ባለአክሲዮኖች የጋራ መሠረተ ልማት ተጠቃሚነትን እና የዲጂታል ክፍያ ግብይቶችን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ውይይት የተደረገበት የካፒታል ጭማሪ በንግድ ሕጉ እና በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት የተዘጋጀ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን የኩባንያውን ካፒታል ወደ ብር 3,017,532,000 የሚያሳድግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ይህም የነባር ባለአክሲዮኖች ቅድሚያ የማግኘት መብት የጠበቀ ሆኖ ቀሪው አክሲዮን በዘርፉ ላይ ለሚገኙ አዳዲስ የፋይናንስ ተቋማት የኩባንያው ባለቤት እንዲሆኑ እድል የሚሰጥ ነው፡፡ የቀረበው የካፒታል ማሳደጊያ ፕሮፖዛልም በኩባንያው ባለአክሲዮኖች ውይይት ከተደረገበት በኋላ ጸድቋል፡፡

 

 

 

ስለኢቲስዊች፦ እ.ኤ.አ. በ2011 የተቋቋመው ኢትስዊች የአክሲዮን ማህበር በሁሉም ባንኮች እና በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ በርካታ ማይክሮፋይናንስድርጅቶች ባለቤትነት የተያዘ ነው። በዋናነት ቀላል፣ ተመጣጣኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀልጣፋ የኢ-ክፍያ መሠረተ ልማት አገልግሎቶችን ለችርቻሮ ክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች ለማቅረብ የተቋቋመ ነው።ከከፍተኛ ክህሎትና ከባለሙያዎች በመደገፍ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችበማቅረብ ላይየሚገኘው ኢትስዊች በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የብሔራዊ ክፍያዎችን ማዘመንና እና ለፋይናንስ አካታችነት አስተዋፅኦ እያደረገ ነው። ከ2016 ጀምሮ በሁሉም ባንኮች የሚሰሩ የኤቲኤም እና የPOS መሳሪይዎች ተናባቢነት እንዲኖር አስችሏል። በአሁኑ ጊዚ ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት የሚደረግን የገንዘብ ዝውውርን ተናባቢ የማድረግ አገልግሎትን ዘርግቷል።

 

ለበለጠ መርጃ የሚከተለውን አድራሻ ይጠቀሙ:

ዮሴፍ እንዳለ፤ ዳሬክተር ማርኬቲንግ እና ኢኖቬሽን ዲፓርትመንት

yosephe@ethswitch.com, +251 955 5569, or Visit our website www.ethswitch.com